በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አራት የጥበቃ አባላት በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተከሰው ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ቅጣት ተጣለባቸው። ጥፋተኛ ከተባሉት ውስጥ በሦስት አባላት ላይ የደሞዝ ቅጣት ተጥሎባቸዋል፤ ከኀላፊነታቸውም አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው እንዲሠሩ ተደርገው የኀላፊነት ክፍያቸውም ተነስቶባቸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ክስ የቀረበባቸው የአስተዳደሩ ሠራተኞች በቀላል የሥነ ምግባር ጥሰት ክስ ተከሰው በማጣራት ሒደት ላይ የሚገኙ 29፣ በከባድ የሥነ ምግባር ጥሰት የተከሱ 7፣ በቀላል የሥነ ምግባር ክስ ተከሰው የተቀጡ 230፣ በከባድ የሥነ ምግባር ክስ ተከሰው በደመወዝ የተቀጡ 15፣ ከሥራ የተሰናበቱ 11፣ ከሥራና ደሞዝ የታገዱ 7 መሆናቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታውቋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011



