ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ ያደጉ ማኅበራት 34 በመቶ ብቻ ናቸው ተባለ

0
838

በመገባደድ ላይ ባለው በጀት ዓመት 200 ሺሕ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ሽግግር ለማድረግ ታስቦ 34 በመቶ የሚሆነውን ብቻ ማሳካት መቻሉ ታወቀ።

የፌዴራል የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጄንሲ እንዳስታወቀው፤ የኢንተርፕራይዞችን ሽግግር በተመለከተ በ2ኛዉ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 200 ሺሕ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ ለማሸጋገር ቢታሰብም በሦስት ዓመት ውስጥ ወደ አነስተኛ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች 67 ሺሕ 16 (34 በመቶ) ብቻ እንደሆኑ አስታውቋል።

ኢንተርፕራይዞችን በየደረጃው በማሸጋገር ለኢንዱስትሪው ልማቱን ከማፋጠን አንጻር የዘርፉ አመራሮች ተግቢውን ትኩረት ማነስ እና የሚሰጣቸው ድጋፍ የዕድገት ደረጃቸውን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ የታዩ ክፍተቶች ናቸው። በመሆኑም በቀጣይ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ በጥቃቅን ደረጃ ያሉት ኢንተርፕራይዞች ወደ አነስተኛ ለማሸጋገር ዕድገት ተኮር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here