10ቱ በገጠር ላሉ ዜጎቻቸው ኤሌክትሪክ የተሻለ አቅርቦት ያላቸው አገራት

0
734

ምንጭ፡-የዓለም ባንክ 2016 (እ.ኤ.አ)

ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚያስችል ሁኔታ ከውሃ ኀይል በሚገኝ ኤሌክትሪክ ምንጮች ላይ የተመሰረተው የኢትዮጵያ የኤሌክትክ የኀይል በገጠር ካሉ ዜጎች ውስጥ 26 በመቶ ለሚያክሉት የሚደርስ እንደሆነ የዓለም ባንክ ሪፖርት ያሳያል። ከ20 ዓመት በፊት ከዜሮ በታች የነበረውን ሽፋን በማሻሻል አሁን ያለው የሽፋን መጠን ላይ የደረሰበት ፍጥነት በተለይም ከ2001 በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት ጨምሯል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

በ1996 የገጠር የኤሌክትሪክ ሽፋን 3.3 ቢገባም በድጋሚ መቀነስ በማሳየት በቀጣዩ ዓመት 1.9 በመቶ ገብቶ፣ ተመልሶ በ1998 ወደ 6.4 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር። በ2001 ባለ ኹለት አኀዝ ዕድገት ውስጥ ገባው የኀይል ሽፋን አቅርቦቱ በ2003 ተመልሶ ወደ 4 በመቶ አሽቆልቁሎም ነበር።

ከፍተኛ የሚባል ዕድገት ሲያሳይ የነበረው የከተማ እና ገጠር የኤሌክትሪክ ሽፋንም ሙሉ ለሙሉ ከታዳሽ የኤሌክሪክ ምንጮች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ እና ለአካባቢ ብክለት ባለው ያነሰ አበርከቶ ምክንያት ሲሞገስ ይሰማል። ነገር ግን ለአየር ንብረት ለውጥ ጫናዎች እና ለተፈጥሮ አደጋዎች ያለው ጫና በሰፊው የሚስተዋል ችግር በመሆኑ አማራጭ የኀይል ምንጮችን የሚከተል ሴክተር እንዲሆን አስተያየቶች ሲሰጡ ሰንብተዋል።

ከአንድ ወር በፊት የታወጀው አገር ዐቀፍ የኀይል ፈረቃም ለግድቦች የውሃ መጠን በከፍተኛ መልኩ መቀነስ ምክንያት ሲሆን ይህም ከዝቅተኛ የዝናብ መጠን እና ከግድቦች በደለል መሞላት ጋር ይያያዛል ተብሎ ይገላፃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here