በጅቡቲ በአሊ አዴ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ 850 የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተመዝግበው በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ታወቀ። በ14 እና በ17 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ታዳጊዎች ከተመዘገቡት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ታዳጊዎች በስደተኞች መጠለያ ጣቢያው ውስጥ ተወልደው ያደጉ ሲሆን ኢትዮጵያን በተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ከሚያዩት የዘለለ እውቀት እንደሌላቸውም ለጀርመን ድምፅ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በጊዜው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ምቹ ባለመሆኑ ስደትን የመረጡ እና በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ዐሥር ዓመታትን ያስቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንም መኖራቸውን እና ወደ አገራቸው ለመመለስም ፅኑ ፍላጎት እንዳላቸው ከጀርመን ድምፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
15 ሺሕ ስደተኞች ተጠልለው የሚገኙበትና በዓይነቱ ትልቁ የሆነው የአዲ ኢሌ ስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ከሱማሌያዊያን እና ከኤርትራዊያን ቀጥሎ ኢትጵያዊያን በብዛት እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታውቋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011


