43 ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

0
1079

በተገባደደው ሳምንት 43 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ። የፀጥታና ፍትሕ የጋራ ግብረ ኀይል ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሰኔ 15/2011 በባሕር ዳርና በአዲስ አበባ በክልልና በፌደራል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ከተሰነዘረው ጥቃት ጋር ተያያዥነት አላቸው ያላቸውን 43 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስገንዝቧል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ግለሰቦች ጋር ኹለት መትረየስ፣ ኻያ ሰባት ክላሽ ጠመንጃዎች እና በርካታ ሽጉጦች ከጥይቶቻቸው ጋር መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን፤ የተለያዩ የጥቃት ማስፈፀሚያ ሰነዶችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በሌላም በኩል ከሰሞኑ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ በባሕር ዳር ከተማ 212 ተጠርጣሪዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፀጥታና ፍትሕ ግብረ ኀይል መግለጫ ያትታል።

ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here