የኤሌክትሪክ አገልገሎት አዲስ የመረጃ አያያዝ ስርዓት መተግበር ጀመረ

0
625

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ1998 ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረውን የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በአዲስ እና በተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት መቀየር የጀመረ ሲሆን ከመጪው ሰኔ 26/2011 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን አዲስ መተግበሪያ መጠቀም ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ። ቀድሞ ከነበረው ስርዓትም ወደ አዲሱ የኢ.አር.ፒ ስርዓት የደንበኞቹን መረጃ በማሸጋገር ላይ በመሆኑ በአብዛኛው የክፍያ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ክፍያ መሰብሰብ ማቆሙም ታውቋል።

ትግበራውን ለማከናወን ዓለም ዐቀፍ ጨረታውን ካሸነፈው ቴክማሂንድራ ከሚባል የሕንድ ኩባንያ ጋር ውል የተገባ ሲሆን የኢ.አር.ፒ ፕሮጀክት በሁሉም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ ዘርፎች ጥቅም ላይ የሚውል ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህም ባሻገር አስፈላጊ የሆኑ የተቋሙ መረጃዎችን ወጥ በሆነ መንገድ ለማደራጀት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል የተባለው ይህ ስርዓት የሰው ኀይል፣ የፋይናንስ፣ የንብረት አስተዳደርና ሌሎችም የሥራ ክፍሎች በመረጃ እጥረትና ግድፈት ምክንያት የሚገጥማቸውን ችግር በማቃለል ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውኑ የሚያግዝ እንደሆነ ገልፀዋል።

አዲሱ ስርዓት የአንድን ተቋም የዕለት ተዕለት ተግባርን ኀላፊነትን እንዲሁም የሥራ ሒደትን የሚያቀላጥፍ እንዲሁም የደንበኞችን እርካታን ለማሻሻል እና የመረጃ ፍሰትን የሚያሳልጥ ሰፊ የሆነ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ሲሆን ይህ ሲስተም በይበልጥ ለማኒፋክቸሪንግ፣ ግዢና አቅርቦት፣ አካውንቲንግ፣ ማርኬቲንግ፣ ደንበኞች አገልግሎት እንዲሁም ለሰው ሀብት አስተዳደር እና የጥራት ቁጥጥር ለመሳሰሉት የሥራ ዘርፎች ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣል።

በተጨማሪም ደንበኞች የሚጠቀሙበትን ሒሳብ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ ከማገዙ በተጨማሪ ክፍያቸውንም በተለያዩ የመክፈያ መንገዶች እንዲፈፅሙ የሚያደርግ እና የተቋሙንም ገቢ ያሳድጋል ተብሎ የሚጠበቅ ቴክኖሎጂ ነው።

ቴክ ማሂንድራ በሕንድ አገር ካሉ የሶፍትዌር አገልግሎት ከሚሰጡ መሰል ኩባንያዎች መካከል በአምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን 3.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዓመታዊ ገቢ ያለው እና 103 ሺሕ 600 በላይ ሞያተኞችን በ90 የተለያዩ አገራት ያሰማራና ኢ. አር .ፒ እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ በመተግበር የዳበረ ልምድ ያለው መሆኑ ታውቋል። ቴክ ማሂንድራ በአፍሪካ ለ60 ደንበኞች አግልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ150 በላይ መሰል ፕሮጀክቶችን አከናውኗል።

ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here