መዝገብ

Author: መሠረት አበጀ

በአዲስ አበባ የወጣቶች ተዘዋወሪ ፈንድ ቆመ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ተጀምሮ የነበረው የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ከኹለት ሳምንት በፊት እንዲቆም ተደረገ። ፈንዱ የቆመበት ምክንያትም እስካሁን በተዘዋዋሪ ፈንዱ የተሰጠውን ገንዘብ ለመለየት እንደሆነ ከተማ አስተዳደሩ ቢገልፅም ወጣቶች ግን ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ከፈንዱ ተጠቃሚ ለመሆን ከሚጠብቁ…

በአንድ ቢሊዮን ብር ገደማ የገበሬዎች ብድር እና ቁጠባ ተቋም ሊመሰረት ነው

በአማራ ክልል የገበሬ ማኅበራት ያለባቸውን የካፒታል እጥረት ለመፍታት በማሰብ ከአባይ ባንክ 972 ሚሊዮን ብር ብድር በመውሰድ የገንዘብ ቁጠባ ፌደሬሽን ለማቋቋም ከብሔራዊ በባንክ ፍቃድ አገኙ። የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፣ የሚመሰረተው ፌዴሬሽን የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራትና የገበሬ ማኅበራት…

ከሰባት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ‹‹የሰው ዘር መገኛ›› የተሰኘ አዲስ ሙዚየም ሊገነባ ነው

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የሰው ዘር ቅሪት አካሎች ለእይታ የሚቀርቡበት አዲስ ሙዚየም በአዲስ አበባ ከተማ አምስት ኪሎ አካባቢ ሊያስገነባ ነው፡፡ በአውሮፓ ህብረት ሙሉ ድጋፍ ከ3 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዲዛይን እና ተያያዥ ስራዎችን ማካሄድ የተጀመረ ሲሆን ጠቅላላ ወጪውም…

የአስጌ ዴንዳሾ የጥበብ ጉዞ በጨረፍታ

“ዴንዳሾ“ በሚለው ነጠላ ዜማው እና በአስደማሚ ሳቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ በቀላሉ መግባት የቻለው አስጌኘው አሻኮ ውልደቱ በደቡባዊቷ የአትዮጵያ ክፍል ጋሞ ጎፋ ሲሆን አስጌኘው አሻኮ ባጋጣሚ ነበር በወላይታ በነበረ ፕሮግራም ላይ ግጥም ሲያቀርብ ዘፋኝ የመሆን እድሉን ያገኘው፡፡ይህንን ችሎታውን በመረዳት የተለያዩ…

የኦሞ ኩራዝ የስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች በሥራ ላይ እያሉ ተገደሉ

በኦሞ ሸለቆ ተፋሰስ ላይ በተገነቡ ኹለት የስኳር ፋብሪካዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት ሠራተኞች በሥራ ላይ እያሉ መገደላቸውና ሠራተኞች የጸጥታ ሥጋት ላይ በመወደቃቸው ፋብሪካው ሥራ እንዳቆመ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሠራተኞች ማኅበር አስታወቀ። በአካባቢው ላይ ያለው የእርስ በእርስ ግጭትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች…

የቀንጢቻ ታንታለም ፋብሪካ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ 132 ሚሊዮን ብር እርዳታ ጠየቀ

ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድረው የቀንጢቻ ታንታለም ፋብሪካ ላለፉት ኹለት ዓመታት ሥራ በማቆሙ ለሠራተኞቹ ደሞዝ እንዲሁም ለሥራ ማስጀመርያ የሚሆን 132 ሚሊዮን ብር ከገንዘብ ሚኒስቴር እርዳታ ጠየቀ። በኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ቡልቲ ወዳጆ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣…

30 የደለል ወርቅ አለኝታ ቦታዎችን ለማግኘት ጥናት ሊደረግ ነው

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ 30 የደለል ወርቅ አለኝታ ቦታዎችን ለመለየት የቅኝት ጥናት በመጀመርያ ዙር በትግራይ፣ በጋምቤላ እንዲሁም በደቡብና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ሊጀመር መሆኑን አስታወቀ። የድርጅቱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ታምሩ መርሻ እንደተናገሩት ተቋሙ የመንግሥት እንደመሆኑ መጠን የመንግሥት ትኩረት አቅጣጫ የሆኑትን የውጪ…

ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ኹለት መቶ ሺሕ ቶን ስንዴ ሊገዛ ነው

መንግሥት ለብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አገልግሎት የሚውል 2 መቶ ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ሊገዛ መሆኑን አስታወቀ። ለብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሚገዛው 2 መቶ ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ እና ችግረኛ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ…

ሀገር ፍቅር ቴአትር

በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉ ቴአትር ቤቶች መካከል የመጀመርያ የሆነው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በመጀመሪያ በ1927 የተቋቋመ ሲሆን በጣልያን ወረራ እና ጦርነት ወቅት የሀገር ፍቅርንና አንድነትን በማቀንቀንና የአርበኝነት ስሜትን በማነሳሳት አገልግሏል። ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ድጋሜ የተመሰረተው ማኅበሩ እጅግ በርካታ የጥበብ ሰዎች፣ ሙዚቀኞች፣…

ቃና ቴሌቭዥን በአንድ ጉዳይ ኹለቴ ልከሰስ አይገባም አለ

የሸማቾች ጥበቃ እና ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ችሎት ቃና ቴሌቪዥንን ጨምሮ ሶስት ተከሳሾች አሳሳች የጥርስ ሳሙና ማስታወቂያ አሰራጭተዋል በሚል ቅጣት መጣሉን ተከትሎ ድርጅቶቹ ለባለስጣኑ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ አሉ። አሳሳች ነው የተባለውን የጥርስ ማስታወቂያ ያዘጋጀው ቢ ሚዲያ እና አሰራጩ ቃና ‹‹ከዚህ…

የአዲስ ዓመት አከባበር ድሮ እና ዘንድሮ

እንደ አበው ተረክ አዲስ ዘመን ሲመጣ ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ዓውደ ዓመት ነው። ከባዱ የኹለት ወራት ጨለማ፣ የክረምቱ ዶፍ ዝናብ፣ አስገምጋሚው መብረቅ፣ ጎርፍና የወንዞች ሙላት ግሳት መስከረም ላይ ይረጋጋሉ። የደመናው መጥቆርና የሰማዩ ልዘንብ ነው የሚል የማስጠንቀቂያ ማጉረምረም ያበቃል። መስኮች ደንና ሸንተረሩ በአበቦች…

ፍርድ ቤቱ ሀያት ቲቺንግ ሆስፒታልን በነፃ አሰናበተ

የሸማቶች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የሀያት ቲቺንግ ሆስፒታል የቀድሞ ባለቤቶች የአክሲዮን ድርሻቸውን ለሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ድንቁ በያሳ እና ወላጅ እናታቸው ዳንሳ ጉርሙ መሸጣቸው ሕገወጥ ውሕደት ነው በሚል ከቀረበባቸው ክስ ኅዳር 28/2011 በነፃ አሰናበታቸው። ግንቦት 26/2011…

መንግሥት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መኪኖችን ሊገዛ ነው

የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የተሸከርካሪ ግዢ ፍላጎት ላቀረቡ የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ 468 ተሽከርካሪዎችን በመጪው ወር መጀመሪያ ለመግዛት ዝግጅቱን አጠናቀቀ። በግዢና ንብረት ማስወገድ በኩል የሚደረገው የተሸከርካሪ ግዢ መንግሥትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሊያደርግበት…

የኑሮ ውድነት ያጠላበት አዲስ ዓመት

የበዐል ሰሞን የገበያ ግርግር መቼም የተለመደ ነው። እንደዚህ ዓይነት ትዕይንት በአዲስ ዓመት ዋዜማም መመልከት እንግዳ ጉዳይ አይደለም። አዲስ ማለዳ በመዲናችን ያሉ የገበያ ማዕከላትን ጎብኝታና ሸማቾችን አነጋግራ እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን በማስተንተን የዕቃዎች ዋጋ ተመልክታ የኑሮን ሁኔታ በአጠቃለይ ለማሳየት ጥረት አድርጋለች።…

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተጨማሪ ኹለት ቋንቋዎች ኅትመት ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከመጪው መስከረም ወር 2012 መጀመሪያ አንስቶ በሶማሊኛ እና በትግሪኛ ቋንቋዎች ኅትመት ለመጀመር ቅድመ ዘግጅቱን አጠናቀቀ። ድርጅቱ መረጃዎቹን በተለያዩ ቋንቋዎች ለሕዝብ ለማድረስ ኹለቱን ቋንቋዎች ጨምሮ ጋዜጦችን ለማሳተም የሰው ኀይል እና የፋይናንስ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን የይዘት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ…

የዋልያዎች ቁጥር በመቶዎች እድገት አሳየ

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እና በራስ ዳሽን ተራራ ላይ ብቻ የሚገኘው ብርቅዬው የዱር እንስሳ ዋልያ ከመጥፋት ስጋት በመውጣት ወደ ዘጠኝ መቶ ከፍ አለ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ ከ 15 ዓመት በፊት የዋልያዎቹ ቁጥር ወደ 150 ማሽቆልቆሉን…

የቀድሞው ዛሚ ሬድዮ እና ኦ.ኤም.ኤን በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

የኦሮምያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት ጀዋር መሀመዱ የሚመራው (ኦ.ኤም.ኤን) ከቀድሞው ዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬድዮ ጣቢያ እና ከአሁኑ የአዋሽ ኤፍ.ኤም ለጊዜው የአየር ሰዓት በመግዛት እንዲሁም በአጭር ግዜ ውስጥ ደግሞ ድርሻ በመግዛት ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ። ከሬዲዮ ጣቢያው ስያሜ…

ለመጪው የገና ዓውደ ርዕይ ኮሜርሻል ኖሚኒስ በታሪክ ከፍተኛውን ዋጋ አቀረበ

በመጪው የገና በዓል በኤግዚቢሽን ማእከል የሚካሄደውን ዓውደ ርዕይ አዘጋጅ ለመለየት ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ ነሐሴ 21 በተደረገው የጨረታ ውድድር ኮሜርሻል ኖሚኒስ 38 ሚሊዮን 395 ሺህ ብር በማቅረብ እና ካለፈው ዓመትም የ12 ሚሊዮን ብር ጭማሪ በማሳየት በኤግዚቢሽን ማእከሉ ታሪክ ከፍተኛ የሚባለውን ዋጋ…

ኃይሌ ገብረሥላሴ ፋውንዴሽን ተቋቋመ

በረጅም ርቀት ሩጫ የኦሎምፒክ ባለድል የሆኑት አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ (ሻለቃ) ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በትምህርት ላይ የሚሠራ ፋውንዴሽን በስማቸው አቋቋሙ። በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማራው ኃይሌ፤ በፋውንዴሽኑ ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ላሉ የትምህርት ተቋማት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ላይ እንደሚያተኩር ገልጾአል።…

ከቱሪዝም የተገኘው ገቢ ቅናሽ አሳየ

በ2011 የበጀት ዓመት ኢትዮጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር አንድ መቶ ሺህ ገደማ ቅናሽ በማሳየት 849 ሺህ ሆኖ መመዝገቡን እና ከእነዚህ ጎብኚዎች የተገኘውም ገቢ በአራት መቶ ሚሊዮን ዶላር ቀንሶ 3.1 ቢሊዮን ዶላር አንደሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በተጠናቀቀው ዓመት ይገኛል የተባለው የውጪ…

የጉደር ፋጦ ግድብ በ950 ሚሊዮን ብር ሊገነባ ነው

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን 950 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የጉደር ፋጦ ወንዝ ላይ ግድብ ስራ ፕሮጀክትን ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል። ኮርፖሬሽኑ ከውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመስኖ ልማት ኮሚሽን ጋር ተፈራርሞ ሥራ ሊጀምር መሆኑን ነው የገለጸው። ከአዲስ አበባ በ150 ኪሎ ሜትር…

የሳውዲ ስታር ምርት በአርባ በመቶ አሽቆለቆለ

ንብረትነቱ የሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን የሆነው ሳውዲ ስታር የሰፋፊ የእርሻ ፕሮጀክት የ2011 ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በ40 በመቶ ቅናሽ ያሳየ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰማች፡፡ ኩባንያው የሚያመርተው አብዛኛው ምርት መቀነሱ የተረጋገጠ ቢሆንም በተለይ የበቆሎና ጥጥ ምርቱ በከፍተኛ…

ኒው ዮርክ ካፌ ሶስት ሚሊዮን ብር ተፈረደበት

ትምህርት ቤቱ ባወጣው አዲስ ጨረታ የካፍቴሪያ ቦታውን ካልዲስ ካፌ ተከራይቶታል ላለፉት ሦስት ዓመታት በክስ ሒደት ላይ የቆየው የአሳይ የሕዝብ ትምህርት ቤት እና የኒው ዮርክ ካፌ ክርክር በሐምሌ ወር 2011 የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ለአሳይ ትምህርት ቤት…

በመዲናዋ በአንድ አመት ውስጥ 115ሺህ የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጠ

በ25 ከተሞች የወሰን ቅየሳ ተካሂዷል በ2010 የበጀት አመት በመላው ሃገሪቱ ከተሰጡ የይዞታ ማረጋገጫዎች ውስጥ ከ 88 በመቶ በላይ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ እንደሆነ የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ። በመላው ኢትዮጲያ ባሉ 23 ከተሞች…

የገቢዎች ሚኒስቴር 20.6 ቢሊየን ብር ውዝፍ ዕዳ ሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ግዜ ከአዲስ አበባ ውጪ ካሉ ሰባት ቅርንጫፎቹ የግብር ዕዳ መረጃን ላይ ተመርኩዞ 20.6 ቢሊዮን ብር ያህሉን መሰብሰቡን ተናግሯል፤ ይህም ከእቅዱ አራት ቢሊዮን ብር በላይ ከመሆኑም ባሻገር ከአጠቃላይ ገቢው 17 በመቶ የሚሆነውን እንደሚሸፍን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። እንደሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ…

በትራፊክ አደጋ የወደመው ንብረት ከእጥፍ በላይ ጭማሪ አሳየ

በ2011 የበጀት አመት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች አማካኝነት የወደመው ንብረት ካለፈው አመት የ815 ሚሊዮን ብር ጭማሪ በማሳየት አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የ113 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ታወቀ። በ2010 የ720 ሚሊዮን ብር ጉዳት የደረሰ ሲሆን በተገባደደው የበጀት አመት በተለይም የቀላል…

የጎዳና ተዳዳሪዎች በዝቅተኛ ደሞዝ ሥራ አንይዝም አሉ

የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመልሶ ማቋቋም ካሰለጠናቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች ውስጥ ከ500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ሥራ ለመግባት የቀረበልን ደመወዝ ዝቅተኛ ነው በማለት ያለሥራ በካምፕ ውስጥ መቀመጣቸውን አስታወቀ። ተማሪዎቹ ሰልጥነው ወደ ሥራ ሲገቡ በዝቅተኛው ደሞዝ ማለትም በ1 ሺሕ 700…

በ3.7 ቢሊዮን ብር አዲስ የአየር ትራንስፖርት ሊመሰረት ነው

የአክስዮን ድርሻው በመጪው ሶስት ወር ውስጥ መሸጥ ይጀመራል አሜሪካን አገር በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በመቀሌ ከተማ መቀመጫውን ያደረገ አዲስ የአየር ትራንስፖርት በ 134 ሚሊዮን ዶላር ለማቋቋም ማሰባቸውን ባሳለፍነው ሳምንት በፕላኔት ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ኖርዝ ስታር የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የአየር…

በትግራይ ክልል የዞን መዋቅርን የሚያስቀር ጥናት ቀረበ

የትግራይ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከ1997 ጀምሮ ሲቀርብ ነበረውን የዞን መዋቅርን የማስቀረት ጥያቄ ለመመለስ ባስጠናው ጥናት መዋቅሩ እንዲቀር ምክረ ሐሳብ መቅረቡ ታወቀ። አብዛኛው የዞን ሥልጣኖች ወደ ወረዳ መውረዳቸውን ተከተሎም ይህ ነው የሚባል ፋይዳ የለውም የተባለው መዋቅር ላይ ለሚኖረው ለውጥም እስከ ወረዳ…

የከተማ አስተዳደሩ የምግብ ዋጋ የሚያንሩት ላይ እርምጃ ወስዳለሁ አለ

በአዲስ አበባ ከተማ በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ የከተማው አስተዳደር ጥናት በማድረግ እርምጃ ሊወስድ መዘጋጀቱን ገለፀ። በተለይም በአትክልት ምርቶች ላይ የታየው ጭማሪ አሳሳቢ እንደሆነ በአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የንግድ ቁጥጥርና ክትትል የሥራ ሒደት መሪ ካሳሁን…

This site is protected by wp-copyrightpro.com