ፍርድ ቤቱ የአምቦ እና የኮካ ውሕደት በድጋሚ ሕገወጥ ነው አለ

0
967

የሸማቾች ጥበቃ እና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት አምቦ ውሃ እና ኮካ ኮላ ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ መሰረት በድጋሚ ተመልክቶ በሰጠው ውሳኔ የቀደመውን ብይን በማፅናት ሕገወጥ ውሕደት በመፈፀም ጥፋተኛ ናቸው ብሏቸዋል።

ከዚህ ቀደም የሥር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለባለሥልጣኑ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተከሳሾች አቤቱታቸውን ባቀረቡት መሰረት የሥር ፍርድ ቤቱ በተነሱት ነጥቦች ላይ በድጋሚ አከራክሮ ውሳኔ እንዲሰጥ አዞ ነበር።

የኮካ ኮላ እናት ድርጅት የሆነው የሆነው ኢስት አፍረካን ቦትሊንግ እና የአምቦ የማዕድን ውሃ ኩባንያ ጥር 2009 በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ (UNECA) አዳራሽ ውስጥ ባካሔዱት ዓመታዊ ጉባኤ ሠራተኞቻቸውን ሰብስበው ውሕደታቸውን ያለ ባለሥልጣኑ ዕውቀት ይፋ አድርገዋል ሲሉ የባለሥልጣኑ ነገረ ፈጆች ክሳቸውን መመስረታቸው ይታወሳል።

ነገረ ፈጆቹ በባለሥልጣኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት ማንኛውም ዓመታዊ ሽያጩ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የንግድ ድርጅት ውሕደት ከመፈፀሙ በፊት ለባለሥልጣኑ በማስታወቅ ባለሥልጣኑ በሸማቾች መብት እንዲሁም በፍትሐዊ ገበያ ውድድር ላይ ያለውን ጫና በማጥናት ፈቃድ ባልስጠበት ሁኔታ መዋሐድ ሕገወጥ ነው በማለት ተከራክሮ ቆይቷል።

ድርጅቶቹም አርማቸውን በማቀላቀል፣ የኮካ ኮላ አከፋፋይ አምቦ ውሃን አብሮ እንዲያከፋፍል በማድረግ እንዲሁም ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ወደ አምቦ የማዕድን ውሃ አራት ሠራተኞችን ማዘዋወሩ ስህተት መሆኑን አሳውቀዋል።

በዚህ መሰረትም ኹለቱ ኩባንዎች ያደረግነው የውሕደት ውል የለም ብለው ሲከራከሩ ቆይተው ለይግባኝ ሰሚ በመጨረሻም ውሕደታቸውን ለኮሜሳ ማሳወቃቸውን ገልፀው የሥር ፍርድ ቤቱም በዚህ መሰረት በሻሻለው መልሳቸው መሰረት እንዲያከራክራቸው ሲሉም አመልክተው ነበር።

የሥር ፍርድ ቤቱም አዲስ በተጨመሩት መከራከሪያዎች መሰረትም ካከራከረ በኋላ ከ10 ወራት በዳኛ መጓደል ምክንያት ፍርዱን ሳይሰጥ ቆይቶ በመጨረሻም በሰኔ 20/ 2011 ቀን በድጋሚ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፍርድ ሰጥቷል። በዋለው ችሎት የኩባንያዎቹ ውሕደት ሕገወጥ በመሆኑ እንዲቆም እንዲሁም ክሱ ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት አጠቃላይ ገቢ 5 በመቶ የገንዘብ ቅጣት እንዲጣልባቸው ወስኗል።

ኩለቱ ኩባንያዎች ድርጊቱ ከተፈፀመበት ዓመት 2009 በፊት ያለው ዓመት ያገኙትን አጠቃላይ ገቢ አምስት በመቶ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ ቅጣት ተጥሎባለቸዋል።

አምቦ የማዕድን ውሃ ከ1922 የተመሰረተ ኩባንያ ሲሆን መንግሥት ወደ ግል ባለቤትነት በተለያዩ ደረጃዎች ያስተላለፈው ሲሆን በመጨረሻም ሳብ ሚለር ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ያስተዳድረዋል። ሳብ ሚለር በደቡብ አፍረካ ከሚገኘው ሳብኮ ጋር ባደረገው ውሕደትም ኮካ ኮላ በቭሬጅን በደቡብ አፍሪካ በጋራ ከአምስት ዓመታት በፊት መመሰረታቸው ይታወቃል።

ሳብኮ የኢስት አፍሪካን ቦትልሊንግስ ከፍተኛውን የሼር ድርሻ የያዘ ድርጅት ሲሆን በተመሳሳይ በ1950ዎቹ በመንግሥት ከተቋቋመ በኋላ ወደግል ይዞታ መዘዋወሩ ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 35 ሰኔ 29 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here