አዲስ አበባ ከአፍሪካ ከተሞች የውድ ሆቴሎች ባለቤት ሆናለች

0
752

መዲናችን አዲስ አበባ በአፍሪካ ካሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ለአንድ አዳር ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈልባቸው ሆቴሎች ያሉባት ከተማ በመሆን ቀዳሚ ሆናለች። የአፍሪካ የንግድ ማኅበረሰብ በድረ ገፁ እንዳስነበበው፤ ከሐምሌ 2010 እስከ ሰኔ 2011 ባለው የጊዜ ገደብ 163 ነጥብ 7 ዶላር (4 ሺሕ 759 ብር ገደማ) በአማካኝ የቀን ወጪ ለመኝታ ብቻ የምታስከፍል ከተማ እንደሆነች ለማወቅ ተችሏል። አማካኝ ገንዘብ መጠኑም ከዓመት ዓመት በ1 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ እያሳየ እንደመጣም ታውቋል።

አዲስ አበባን በማስቀደም በኹለተኛ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ የጋናዋ ዋና ከተማ አክራ በ160 ነጥብ 3 ዶላር የሚያስከፍሉ ሆቴሎች ባለቤት ስትሆን የናይጀሪያዋ ትልቅ የንግድ ከተማ ሌጎስ በሦስተኛ ደረጃ 132 ነጥብ 5 ዶላር የአንድ አዳር የሆቴል ወጪ በማስከፈል በሦስተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች።

መቀመጫውን አሜሪካን አገር ያደረገው እና በዋነኛነት የጉዞ ጥናታዊ ጽሑፎችን የሚያጠናቅረው “ስሚዝ ትራቭል ሪሰርች” በፍጥነት እያደገ የሚገኝ ምጣኔ ሀብት፣ ስኬታማ አየር መንገድ እንዲሁም የዓለምቀፍ ማኅበረሰብ መቀመጫ መሆኗ ለአዲስ አበባ የሆቴል ዘርፍ ዕድገት ምክንያት ነው ብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here