በኢንዱስትሪ ፓርኮች የኀይል አቅርቦት ከግማሽ በታች ነው ተባለ

0
668

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንነሐሴ 2/2011 ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት የኀይል አቅርቦት ችግር እንዳለበት የኀይል አቅርቦት ችግሩ ፓርኮቹ በሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዳይሠሩ እክል እንደፈጠረ ገልጿል።

በሥራ ላይ ለሚገኙ ፓርኮች ከተጠየቅው 306 ሜጋ ዋት ኀይል ውስጥ እየቀረበ ያለው 145 ሜጋ ዋት ሲሆን በግንባታ ላይ ያሉት ተጠናቀው ወደ ሥራ ሲገቡ በዘላቂነት 1719 ሜጋ ዋት ኀይል ያስፈልጋቸዋል።

የኀይል አቅርቦት ችግሩ የውጭ ኢንቨስትመነትን ከመሳብ አንጻር አሉታዊ ገጽታ ሊፈጥር እንደሚችልና ችግሩን ለመፈታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋግሩ ከመሆኑም በተጨማሪም ፓርኮቹ የራሳቸውን ኀይል አማራጮች እንዲፈጥሩ እየተሠራ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተግለጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባለፈው በጀት ዓመት 110 ሚሊየን ዶላር የኤክስፖርት ገቢና ከ 90 ሺሕ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here