‹‹አፍሪካዊያን ሴቶች ኮድ ማድረግ ይችላሉ እንቅስቃሴ›› ተጠናቀቀ

0
514

ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት በአዲስ አበባ አፍሪካ ኅብረት ጊቢ ውስጥ ሲሰጥ የነበረው ወጣት ሴቶችን በቴኖሎጂ የማብቃት እንቅስቃሴ ትናንት አርብ ነሐሴ10/2011 ተጠናቋል።

ከአዲስ አበባ ከተለያዩ መንግሥት ትምሕርት ቤቶች የተወጣጡ 150 የኹለተኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎችን ያካተተው ስልጠናው፥ ከመሰረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀት እስከ ከፍተኛ የኮምፒውተር ቋንቋን እስከመፃፍ የሚደርስ ስልጠና እንዳገኙም ታውቋል ። በተባበሩት መንግስታት የሴቶች ድርጅት (ዩኤን ውሜን) አማካኝነት ለሦስተኛ ዙር የተዘጋጀው ይኸው ስልጠና በርካታ ወጣት ሴቶችን በማብቃት ሴቶች ከቴክኖሎጂ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት እንደሚያሻሽል ተጠቁሟል። ሰልጣኞቹ ወደ ቤታቸው ሲመለሱም ለእያንዳንዳቸው በነፍስ ወከፍ አንዳንድ ላፕቶፕ ኮሚፒውተሮችን በስጦታ መልክ እንደሚሰጣቸው ታውቋል።

ዩኤን ውመን በዋናነት ሥልጠናውን ያዘጋጀው ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘው የዴንማርክ ኢምባሲ፣ ዓለም ዐቀፉ የቴሌኮም ድርጅት እንዲሁም አፍሪካ ኅብረት ግንባር ቀደም አጋዦች እንደነበሩም አዲስ ማለዳ ከዩኤን ውመን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here