ከሩብ ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

0
531

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ በ300 ሚሊዮን ዶላር የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ እንደሆነ ታወቀ። በአንድ መቶ ሺሕ ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የኢንዱስትሪ መንደሩ የግንባታው ወጪን በሚመለከት 15 በመቶ ከኢትዮጵያ መንግሥት ሲሆን ቀሪው 85 በመቶ ደግሞ ከቻይና መንግሥት ጋር በተደረሰ ብድር ስምምነት መሰረት በዝቅተኛ ወለድ የሚከፈል እንደሆነ ተጠቁሟል።

የኢንዱስትሪ መንደሩን ግንባታ በዋናነት የሚያከናውነው የቻይናው ሲቪል ምሕንድስና ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ሲሲኢ ሲሲ) ሲሆን የግንባታ ድርጅቱ ከዚህ ቀደም አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን በ146 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገንብቶ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው። አዲሱ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታው ሲጀመር ለ2600 ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ደግሞ በአምራች ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ልዩ መስህብ ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል። በአሁኑ ሰዓት ከመሬት ይዞታ እና ከገንዘብ ወጪዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሒደት ላይ እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here