9 ኪሎ ግራም ወርቅ ይዞ ከአገር ሊወጣ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

0
905

ባሳለፍነው ሳምንት አንድ ግለሰብ ዘጠኝ ኪሎ ወርቅ በህገወጥ መንገድ በሶማሌ ክልል በኩል ከአገር ለማስወጣት ሲሞክር በብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ረጅም ክትትል በቦምባስ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ግለሰቡ ከአገር ይዞ ሊወጣ ሲል ከተያዘው ወርቅ በተጨማሪ ሌሎች የተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦችም ይዞ ነበር ሲሉ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም አርባ አንድ ሺህ ዶላር እና 55ሺህ የሳውዲ ሪያል በተቀያሪ ጫማዎቹ ውስጥ ይዞ ነበር ሲሉ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

ከአምስት አመት በፊት ከወርቅ የወጪ ንግድ ከአራት መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ባለፈው አመት ከዘርፉ የተገኘው ገቢ ግን ወደ 30 ሚሊየን ዶላር ማሽቆልቆሉን የማአድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡ በሁሉም የወርቅ አምራች ክልሎች የኮንትሮባንድና ሕገ ወጥ ንግድ መስፋፋት ለዘርፉ መዳከም ከፍተኛ አስተዋቅኦ አድርገዋል ተብሏል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here