ከዘጠኝ ወራት በፊት ከደቡብ ክልል ሸካ ዞን የኪ ወረዳ በመፈናቀል በቴፒ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገለጹ።
በከተማዋ የሚገኙ ተፈናቃዮችም ወደ ቀድሞ ቀዬቸው ለመመለስ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ቀደም ሲል በመንደሮቹ የግድያ ፣ የዘረፋና የመፈናቀል ድርጊት የፈጸሙ ግለሰቦች እስከአሁን ለሕግ ባለመቅረባቸው ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት ሊያደርሱብን ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የአካባቢው ባለስልጣናት በበኩላቸውም የተፋናቃዮቹን ቅሬታና ስጋት ለመቅረፉ የሚያስችሉ ሥራዎችን በማከናውን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011


