የአየር ብክለት በዓመት 9 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል

0
1033

በዓለም ዙሪያ ሁሉን ዓይነት የከባቢ አየር ብክለት በየዓመቱ ለ9 ሚሊዮን ሰዎች ኅልፈት ምክንያት መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ።
55 ከመቶ ብክለቱ ከአነስተኛ እና ከባድ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ከሚለቀቅ ቆሻሻ አየር የሚመነጭ መሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል።
ዩናይትድ ስቴትስ ሙሉ ለሙሉ ከበለጸጉ አገራት መካከል በብክለት በርካቶችን በማጣት ሰባተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በብክለት በርካቶችን በማጣት ባንግላዴሽ እና ኢትዮጵያም ዩናይትድ ስቴትስን ከመሀል አድርገው እንደሰፈሩ ተዘግቧል።
እንደ ጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር በ2019 ብቻ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከ140 ሺሕ በላይ ሰዎች በአየር ብክለት ሕይወታቸውን አጥተዋል ነው የተባለው። ዘመናዊ የአየር ብክለት ላለፉት 20 ዓመታት በአዳጊ አገራት መጨመሩ ቢታይም፣ በዩናይትድ ስቴትስ፤ የአውሮፓ ኅብረት እና ኢትዮጵያ ግን ቁጥሩ መቀነስ ማሳየቱም ተጠቅሷል።
ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ከቤት ውጪ የአየር ብክለት እንዲቀንስ እንዲሁም በንፅህና አጠባበቅ ዘርፍ መሻሻል እንዲኖር በመሥራታቸው ጥናቱ በተደረገበት ወቅት በአየር ብክለት የሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገልጧል።
ከኢትዮጵያ የተገኘው ጥናት ግን ምናልባትም በአዘጋገብ ጉዳዮች የተነሳ በተፈለገው መልኩ በደንብ ሊብራራ የሚችል እንዳልሆነ በጥናቱ ተገልጧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 185 ግንቦት 13 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here