መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበምሥራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በምሥራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በድርቅ በተጠቁት ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ የተከሰተው የረሃብ አደጋን ዓለም ችላ እንዳለው ኦክስፋም እና ሴቭ ዘ ቺልድረን ባወጡት ሪፖርት አስታውቀዋል።
በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ረሃብ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ያለው ሪፖርቱ፣ በኬንያ 3.5 ሚሊዮን ሰዎች በከፍተኛ ረሃብ እየተሰቃዩ ነው ብሏል።
በሦስቱ አገራት ለከፍተኛ ረሃብ የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረበት ከ10 ሚሊዮን ወደ 23 ሚሊዮን አድጓል የተባለ ሲሆን፣ እ.አ.አ በ2011 በሶማሊያ ከ260 ሺሕ በላይ ሰዎችን ከገደለው ረሃብ ጋር ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት ሪፖርቱ ስጋቱን አስቀምጧል።
በሪፖርቱ ዓለም መከላከል የሚቻለውን ተደጋጋሚ አደጋዎች መከላከል አለመቻሉን አጉልቶ ያሳያል የተባለ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ለቀረበው አስቸኳይ ድጋፍ “በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ” የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ዝቅተኛ ነው ተብሏል።
በሪፖርቱ መሠረት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰተ ድርቅ፤ በግጭቶች ምክንያት ሰዎች ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀላቸውና የኮቪድ-19 ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የተነሳ፣ ሰዎች ችግሩን እንዳይቋቋሙ አድርጓል። የዩክሬንና የሩስያ ጦርነትም እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዋጋ በማናር የረሃብ አደጋውን ይበልጥ አወሳስቦታል የተባለ ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ቢሰጡም የዓለም መሪዎች በጣም ከመዘግየታቸው ሌላ የሰጡት ምላሽ አነስተኛ ነው መባሉ ተሰምቷል።
በምሥራቅ አፍሪካ ለወራት የዘለቀው ድርቅ ያስከተለው ጉዳት መጠን እስካሁን በትክክል የታወቀ ባይሆንም፣ በየጊዜው የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመላክቱት በርካቶች መሞታቸውን ነው። ሕይወታቸውን የሚገፉባቸውን እንስሳት በድርቁ ምክንያት ያጡም እጅግ በጣም ብዙ መሆናቸው ሲነገር ቆይቷል። በድርቁ ሳቢያ በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ብዙዎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ሊሰጣቸው ይገባ የነበረ ትኩረት በዓለም ዐቀፍ ደረጃም ይሁን በመንግሥት በኩል ዝቅተኛ መሆኑ ይነገራል።


ቅጽ 4 ቁጥር 185 ግንቦት 13 2014

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች