በምዕራብ ጎጃም ዞን ከ595 በላይ ተጠርጣሪዎች ለሕግ ቀረቡ

0
1193

አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) እየተወሰደ ባለው ሕግ የማስከበር እርምጃ 595 ተጠርጣሪዎችን ለሕግ ማቅረቡን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ መልካሙ ተሾመ በሰጡት መግለጫ፤ በዞኑ በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጹ የፀጥታ ችግሮችና የሰላምና ደህንነት መስተጓጉሎች አጋጥሞ መቆየቱን ተናግረዋል።

ግድያ፣ መኪና አስቁሞ ዘረፋ፣ ልዩ ልዩ ሥርቆት፣ ህገ ወጥ ጥይት ተኩስ፣ የጦር መሳሪያ ንግድ፣ ኩንትሮባንድ እና የመሳሰሉት የወንጀል ድርጊቶች በመበራከታቸው የሕዝቡ ሰላምና ደህንነት አደጋ ውስጥ ቆይቷል ብለዋል።

አገራዊ አንድነትን ለማምጣትና የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እንደ አገር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አሁን ላይ በዞኑ በኹሉም አካባቢዎች ሕግ የማስከበር ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ሕግ ማስከበር ተግባርም በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፎ አለው ተብሎ የሚጠረጠር ማንኛውም ግለሰብ ያለምንም ልዩነት በሕግ ጥላ ሥር እንዲውል ተደርጎ ምርመራ በመደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ሕግ የማስከበር ተግባሩ በሕዝቡ ፍላጎትና አጋዥነት እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው እየተከናወነ ባለው ሕግ የማስከበር ተግባር 595 ተጠርጣሪዎችን በሕግ ጥላ ስር በማዋል ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል። ሂደቱም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመፈጸም ላይ ይገኛል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የሕዝቡን መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረው የሕግ ማስከበር ተግባሩ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ ለሰላም ማስከበሩ እያደረገ ያለውን አጋርነት አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥል ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here