በሳምንት ለ240 ሺህ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለለት የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ዛሬ ተመርቆ ሥራ ይጀምራል

0
909

ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና በሳምንት ለ240 ሺህ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ማዕከሉ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው።

ቀድሞ ይሰጥ ከነበረው አገልግሎት በአምስት እጥፍ በማሳደግ ወደ ሥራ የገባውና በከተማ አስተዳደሩና በአብ ሜዲካል ሴንተር በትብብር የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ለምረቃ እንደሚበቃም ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ፤ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።

   

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here