መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየኢትዮጵያ አየር መንገድ ከምርጥ የአፍሪካ ተቋማት አንዱ ሆኖ ተመረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከምርጥ የአፍሪካ ተቋማት አንዱ ሆኖ ተመረጠ

ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከምርጥ የአፍሪካ ተቋማት መካከል አንዱ በመሆን የሦስተኛ ደረጃን አገኘ፡፡

አየር መንገዱ የተመረጠው “በአፍሪካ ምርጥ ብራንዶች” ዘርፍ የሆነው የብራንድ አፍሪካ የ2022 የደረጃ አሰጣጥ በናይጄሪያ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ኤም.ቲ.ኤን እና ዳንጎቴ ከአፍሪካ ምርጥ ብራንዶች ውስጥ የቀዳሚነቱንና ኹለተኛውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

አየር መንገዱ “ሦስት የአፍሪካ ኩራት ብራንዶች” በሚለው ዘርፍ ኹለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በዚሁ ዘርፍም የናይጄሪያው ዳንጎቴ አንደኛ እንዲሁም ኤም.ቲ.ኤን ሦስተኛ ደረጃን መያዙን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

ኤም.ቲ.ኤን ዋና መሥሪያ ቤቱን በደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ ያደረገና በተለያዩ አገራት ላይ የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች