የተባበሩት መንግስታት በኦሮሚያና በጋምቤላ ድጋፍ ለማድረግ መቸገሩን ገለጸ

0
652

በምዕራብ ኦሮሚያና በጋምቤላ ክልሎች በተፈጠሩ ተደጋጋሚ ግጭቶች ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የምግብና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ መቸገሩን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በሐምሌ ወር ብቻ ከ276 በላይ ግጭቶች በኹለቱ ክልሎች የተከሰቱ መሆኑን በሪፖርቱ የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ ከ197 በላይ ግጭቶች በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ በተመሳሳይ ወቅት መቀስቀሳቸውን አስታውቋል። በተለይም መንግሥት ባደረገው ተፈናቃዮችን በአፋጣኝ ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ሥራ ላጋጠመው የሰብዓዊ እርዳታ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት መቸገሩን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

ለአብነትም በምዕራብ ወለጋ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው ካማሺ ዞን ቢመለሱም ባጋጠማቸው የደኅንነት ስጋት በድጋሚ ተፈናቅለዋል። ለተፈናቃዮቹም እርዳታ በጽሕፈት ቤቱ አጋሮች በኩል ለማቅረብ ችግር ማጋጠሙንም አክሎአል። በተጨማሪም በነጆ ከተማ ተፈናቃዮች ባጋጠማቸው ችግር የተነሳ ሕይወታቸውን በወሲብ ንግድና በህጻናት ዝውውር ላይ እንዲመሩ መገደዳቸውን ጽሕፈት ቤቱ አውስቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 46 መስከረም 10 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here