የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በመጪው ጥቅምት ወር በኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ጉብኝት እንደሚኖራቸው ታውቋል። የፀጥታ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ጄሪ ማቲጂላን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ሱዳ ትሪቡን ምክር ቤቱ በመጪው ጥቅምት 12 እና 13 በአዲስ አበባ በመገኘት ከአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ምክር ቤት ጋር ምክክር ለማድረግ ቀጠሮ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
ምክር ቤቱ አባላት በጥቅምት 14 ወደ ደቡብ ሱዳን በማቅናት በዋና ከተማዋ ጁባ በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካን አምባሳደር ኬሊ ክራፍት ጋር በመገናኘት የአንድ ቀን ጉብኝት እንደሚኖራቸው ታውቋል። የደቡብ ሱዳ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ታባን ዴንግ ባሳለፍነው ሳምንት በ74ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በኅዳር ወር ላይ በደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት እንደሚመሰረት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የተደረገ ጉብኝት እንደሆነ ተገልጿል። የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የሚኖራቸው የጉብኝት መርሃ ግብር በጥቅምት 15 እንደሚጠናቀቅ እና በቀጣዩ ቀን ወደ ኒው ዮርክ እንደሚያመሩ መርሃ ግብሩ ያመላክታል።



