ዳሰሳ ዘ ማለዳ ማክሰኞ መስከረም 20/2012

0
722

1-በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ መስከረም 20/2012 በይፋ ተጀምሯል።አጠቃላይ 56 ኪሎ ሜትር ከሚሆነው የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በቻይና መንግሥት የሚደገፈው 12 ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ሲሆን በኹለት ዙር ተሰርቶ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………

2-የቤተ መንግሥት ዕድሳት በቀጣይ ሳምንት ሐሙስ መስከረም 29/2012 ዓ.ም ተጠናቅቆ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረገ ተገልጿል።በማግስቱ ዓርብ ማለትም መስከረም 30/2012 ዓ.ም የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ቤተ መንግሥቱን እንደሚጎበኙም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።ከሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3/2012 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር በመክፈል ቤተ መንግሥቱን መጎብኘት እንደሚችልም ነው የተገለፀው።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………

3-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን በዛሬ መስከረም 20/2012 በይፋ አስጀምራል።ፕሮጀክቱ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30 እስከ 45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት ያለው ሲሆን የመንገድ ግንባታውን ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ የተባለ የስራ ተቋራጭ የሚያከናውነው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………

4-ሰባተኛው የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽን ጉባኤ በሩስያ ፒተርሰበርግ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።በጉባኤው የንግድ ትብብር፣ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአማራጭ የኃይል ምንጮች፣ የህዋ ቴክኖሎጂ፣ የዲጅታል ቴክኖሎጅ መገናኛ ዘዴዎች፣ የባህልና ቱሪዝምና ሌሎች አዳዲስ የትብብር ማዕቀፎችና የትኩረት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ዝርዝር ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………

5-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን ልዩ መልዕክተኛ  በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዩ መልዕክተኛው  በተለያዩ የኹለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሒደዋል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………

6- በአፋር ክልል ዞን ሶስት ወረር ውስጥ ልዩ ስሙ አምባሽ በሚባል ስፍራ1702 ኪግ የሚመዝን ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ ከሕብረተሰቡ የደረሰ ጥቆማን መሰረት በማድረግ በአዋሽ ጉምሩክ ቅርንቻፍ ጽሕፈት ቤት የመረጃ ሰራተኞች እና ፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት ከፍተኛ ክትትል በቁጥጥር ስር ዉሏል።(ዋልታ)

………………………………………………

7–የኢትዮጵያ ኅይማኖት ተቋማት ጉባኤ 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉባኤው ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ፥ ጉባኤው በሰላምና በመከባበር እሴት ግንባታ የሚሰራቸውን ስራዎች ይበልጥ ወደ ሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………

8-በዶሃዉ  17ኛው ዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮን ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ የማራቶን አትሌቶች በሙሉ ለጤንነትና ለአስተዳደራዊ አሠራር ሲባል ከ3 ወር በፊት ምንም ዓይነት ውድድር ማድረግ እንደሌለባቸው በዶሃ የተገኘው የፌዴሬሽኑ አመራር ወሰነ።በዶሃ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ሁሉም ኢትዮጵያን የወከሉ ሴት አትሌቶች ውድድሩን በሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው መገለጹ የሚታወስ ነው።(ኢቢሲ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here