ለ21 ዓመታት በኔዘርላንድ ተደብቆ የነበረው ኢትዮጵያ ንብረት የሆነው ዘውድ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ ነው

የ18ኛው ክፍለ ዘመን ዋጋ የማይገዛው ድንቅ ቅርስ የተባለለት እና ከ21 ዓመታት በፊት ተሰርቆ ወደ ኔዘርላን በማምራት ተደብቆ የነበረው ዘውድ ለኢትዮጵያ ተላልፎ ሊሰጥ ነው። ለኹለት አስርት ኣመታት በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቆ እንደነበረ የተነገረለት ዘውድ እየሱስ ክርስቶስ እና የአስራ ኹለቱን ሐዋሪያት ምስል የተቀረጸበት እንደሆነም ተነግሯል።

በያኔው ስደተኛ እና በአሁኑ የስራ ኣመራር አማካሪ ሲራክ አስፋው ለኻያ አንድ ዓመታት በቦርሳ ውስጥ ተቀምጦ የነበረው ዘውድ ኢትዮጵያ ታላላቅ የስራ ኃላፊዎች እና አመራሮች በተገኙበት እንደሚተላለፍ ለማወቅ ተችሏል። በ1960ዎቹ የነበረውን የቀይ ሽብር እንቅስቃሴ በመሸሽ ለስደት የተዳረጉት ሲራክ አስፋው ከኻያ ዓመታ በፊት በቦርሳ ውስጥ እንደተቀመጠ ቅርሱን እንዳገኙት እና ወደ ሚኖሩበት ቤት ወስደው እንደደበቁት  ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here