በተመረጡ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ስደተኞችና ወጣቶች ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚሰራው ኤ.ኢ.ሲ ኢትዮጵያ፣ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ የአገርን ኢኮኖሚ ከፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።
የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የስራ ስምሪትና የገበያ ዘርፍ ሚንስትር ደኤታ ንጉሱ ጥላሁን፣ የስራ አጥነት መጠን ስምንት ነጥብ ስምንት በመቶ መድረሱንና በየአመቱም ተመራቂ ወጣቶች ገበያውን እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ እንደዚህ የስራ አጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና ይኖረዋልም ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ካሉ ተፈናቃዮች በተጨማሪ ከ800ሺ በላይ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች እንደምትገኝ ጠቁመዋል። ኤ.ኢ.ሲ ኬንያና ሩዋንዳን ጨምሮ በተመረጡ ስምንት የአፍሪካ አገራት ላይ የሚሰራ ድርጅት ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በስራ ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግ በአሶሳና በጂግጂጋ ለ250ሺህ የሚደርሱ ጥቃቅና አነስተኛ ስራ ፈጣሪዎችን አቅም ለመፍጠር እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
ቅጽ 4 ቁጥር 190 ሰኔ 18 2014



