ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ በነጻ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው

0
1067

የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመጪው የትምህርት ዘመን ምገባ በሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ በነጻ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

የንጽህና መጠበቂያው ለሴት ተማሪዎች በነጻ እንዲሰጥ በአዋጅ የተፈቀደ መሆኑንና ይህንን በአዋጅ የተፈቀደ መብት ተግባራዊ ለማድረግ ከምገባ ኤጀንሲ ጋር በመሆን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው ቢሮው ያስገነዘበው፡፡ ይህ እገዛ የሴት ተማሪዎች የትምህርት ማቋረጥና የመቅረት መጠን በከፍተኛ መጠን እንደሚቀንስም ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይም፣ ቢሮው የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ ለማድረግም ከጉምሩክ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በየጊዜው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ ይህም ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን መጠቀም ካልቻሉ ጫናው በጣም ሰፊ መሆኑ ይነገራል፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በህግ ማዕቀፍ ዙሪያ ለሴቶች ጥቃት ተከላካይ ኮሚቴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና የወሰዱ ኮሚቴዎችንም በዚሁ ሳምንት አስመርቋል። ቢሮው የሴቶች ጥቃትን ለመከላከል፣ ሴቶችን ለማብቃት እና መሰል ጉዳዮችን በሚመለከት በርካታ ስራዎችን ማከናወኑንም ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡


ቅጽ 4 ቁጥር 190 ሰኔ 18 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here