በጎርፍ ምክንያት ዘጠኝ የውሃ ጉድጓዶች ምርት መስጠት ማቆማቸው ተነገረ

0
829

የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን እንደገለፀው፣ የክረምቱ ዝናብ መጨመር ጋር ተያይዞ በአቃቂ ከርሰ ምድር ከሚገኙ የውሃ ጉድጓዶች መካከል 30 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውሃ የማምረት አቅም ያላቸው ዘጠኝ የውሃ ጉድጓዶች ምርት መስጠት ማቆማቸው ተነግሯል።

ከእነዚህም አራቱ ጉድጓዶች የመዳረሻ መንገዳቸው በጎርፍ በመዘጋታቸው እና የኤሌክትሪክ መስመር ብልሽትን መጠገን ባለመቻሉ የውሃ ምርታቸው መቋረጡን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።

ባጋጠመው የውሃ ምርት መስተጓጎልም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከወረዳ አንድ እስከ 12፣ እንዲሁም 13 እና 14፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ከወረዳ አንድ እስከ ሰባት የውሃ እጥረት ይገጥማቸዋል ተብሏል።

በተጨማሪ ወረዳ ዘጠኝ፣ 10፣ 11 በከፊል፣ አቃቂ ክፍለ ከተማ ከወረዳ አራት እስከ ስምንት፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 እንዲሁም አንድ እና ኹለት በከፊል፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ከወረዳ አንድ እስከ ሰባት እና ወረዳ 9፣ ልደታ ከወረዳ አንድ እስከ አራት እንዲሁም ከስምንት እስከ 10፣ አዲስ ከተማ ወረዳ ኹለት እና ሦስት የውሃ እጥረት ችግር እንደሚገጥማቸው ባለሥልጣኑ ተናግሯል።

ባለሥልጣኑ በጊዜያዊነት የውሃ ችግር የገጠማቸውን የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ ፈረቃ በማስተካከል ለማዳረስ ጥረት የሚያደርግ ይሆናል ነው የተባለው።

ባለሥልጣኑ አሁን ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚያደርገው በተጨማሪ በቀጣይ ዓመትም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ጉድጓዶችን በመለየት ጉዳቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመቅረፍ እንደሚሠራም ጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 198 ነሐሴ 14 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here