የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ

0
5658

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለውን ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም መወሰኑን አስታውቋል።

ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይ ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውሷል። ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ ዓመት ተግባራዊ ተደርጎ መቆየቱንም ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ከቤት ኪራይ ጭማሪ ጋር ያለው ችግር ስላልተቀረፈ እንዲሁም አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት በማስገባት፣ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም መወሰኑን ገልጿል።

በመሆኑም ይህንን ክልከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማኅበረሰቡ ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል አስታውቋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 199 ነሐሴ 21 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here