አገልግሎቱ 8 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የጭነት አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ

0
806

በ2014 በጀት ዓመት ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን በላይ የማጓጓዝ አገልግሎት መስጠቱን የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኀን በሰጠው መግለጫ፣ የሥራ ዘመኑ በበርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ችግሮች መኖር በተግባራቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮበት እንደነበር ገልጿል።
በተለይም የሩስያና የዩክሬን ጦርነት፣ የዋጋ ንረት፣ በቻይና ወደብ ቀጠና ያልቀነሰው የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዲሁም የአገር ውስጥ የፀጥታ ጉዳዮች ፈታኝ ነበሩ ብሏል።

ድርጅቱ በሥራው ላይ ችግሮች ቢገጥሙትም በበጀት ዓመቱ ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን በላይ የማጓጓዝ አገልግሎት መስጠቱን ገልጿል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን ብቻ ማስገባት መቻሉ ተጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 199 ነሐሴ 21 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here