አምስት የደች አበባ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ለመሰማራት ተስማሙ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ልዩ ስሙ ቁንዝላ በተባለ አካባቢ አምስት ደች አበባ አምራች ድርጅቶች በ500 ሔክታር ላይ የአበባ እርሻ ለማልማት ስምምነት ላይ ደረሱ። ስምምነቱ ይፋ የሆነው አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከኔዘርላንድ አምባሳደር ጋር ባደረጉት ውይይት ነበር።

አምባሳደር ቤንት ቫን በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት መንግስታቸው የአበባ እርሻ በሚገነባባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ማቋቋሚያ የሚውል 20 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚለግስም አስታውቀዋል። ይህም 10 ሽሕ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርም በበኩላቸው መንግስት የአካባቢውን እና የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ክልሉን የኢንቨስትመንት መስህብ ለማድረግ እንደሚሰሩም ማስታወቃቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here