የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ18 ዓመታት በላይ አቋርጦት የነበረውን በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ18 ዓመታት አቋርጦት የነበረውን ወደ ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ያደርግ የነበረውን የቀጥታ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። አየር መንገዱ  እየተገባደደ ባለው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ እና አዲሱ ዓመት መባቻ ላይ በረራውን እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል።

ከ18 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ጥንታዊቷ አውሮፓዊት አገር ግሪክ የሚደረገው በረራ አየር መንገዱ በአውሮፓ ያሉትን መዳረሻዎቹን ወደ 20 ከፍ ያደርግለታል ተብሎ ተጠብቋል። በቅንጡዎቹ የቦይንግ ምርቶች 787 ድሪም ላይነር ወደ ግሪክ አቴንስ የሚደረገው በረራ በሳምንት ሦስት ቀናት የበረራ ሰሌዳ ተይዞለታል።

በጎብኝዎች መዳረሻነት ከአውሮፓ ከተሞች በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀሰው አቴንስ የዲሞክራሲ ትውልድ ቦታ በመባልም ትሞካሻለች። ተቋርጦ የነበረውን በረራ መጀመር አስመልክቶ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማሪያም እንደተናገሩት፤ በቀጥታ በረራ ወደ ግሪክ መመለሳችን ደስታ ይሰጠናል ካሉ በኋላ ግሪክ አቴንስ ከመቼውም በላይ ለአፍሪካ የምትቀርብበት ጊዜ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የሚጀመረውን ከአዲስ አበባ ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ጨምሮ 126 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here