እስራኤል ለኢትዮጵያ የአየር መቃወሚያ ለግሳለች መባሏን አስተባበለች

0
377

እስራኤል ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ለመጠበቅ ለኢትዮጵያ የአየር መቃወሚያ መሳሪያ በዕርዳታ መልክ ሰጥታለች መባሉን አስተባበለች። በግብጽ ካይሮ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ እንዳስታወቀው፤ ጺዮናዊያን ለኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባውን ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ለመጠበቅ የአየር መቃወሚያ ረድታለች ተብሎ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የተዘገበው ዜና ከእውነት የራቀ ነው ሲል አስተባብሏል።

ኤምባሲው በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ የእስራኤል የአየር ጥቃት መከላከያ መሳሪያ በኢትዮጵያ ያውም በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ላይ መተከሉን በሚመለከት በርካታ ወሬዎች ሲሰሙ መቆየታቸውን ገልጾ፤  የተባሉት ወሬዎች በሙሉ ከአሉባልታ የዘለሉ እንዳልሆኑና ፍፁም የሐሰት መረጃዎች መሆናቸውን አስነብቧል።

የግብጽ መንግሥት የኅዳሴው ግድብን በሚመለከት ግድቡ ግብጽ ከዓባይ ውሃ የምታገኘውን የውሃ ድርሻ በእጅጉ የሚቀንስ ነው ሲል መቆየቱ የሚታወስ ነው። የእስራኤል መንግሥትም ኢትዮጵያ እና ግብጽ ግድቡን በሚመለከት  በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በቶሎ እንዲያረግቡ ፅኑ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here