የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አልነበረም ሲሉ ገለፁ

የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአስተዳደር ዘመናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት የሰብኣዊ መብት ጥሰት እንዳልነበር ገለፁ። ኃይለማሪያም ከጀርመን ድምጽ ዶቼ ቬለ በእንግሊዘኛው ክፍል ኮንፍሊክት ዞን በሚል መርሃ ግብር ከቲም ሴባስቲያን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአስተዳደር ዘመናቸው የሚያውቁትና በእርሳቸው እውቅና የተደረገ ሰብኣዊ መብት ጥሰት እንዳልነበር ተናግረዋል።

በስድስት ዓመታት ቆይታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የፀጥታ አካላት በየቦታው የሚያደርሱትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት በዓለም አቀፍ ደረጃ ይታወቅ እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄም ‹‹በእርግጥ ባውቅ ኖሮ አስተካክለው ነበር›› ሲሉ ተደምጠዋል። ኃይለማሪያም አያይዘውም በእርሳቸው የመጨረሻ የስልጣን ዘመን በርካታ በሕግ ጥላ ስር የነበሩ ሰዎች መለቀቃቸውን እና ይህም በስልጣን ዘመናቸው በበጎ ጎን ሊነሳ የሚገባው ጉዳይ እንደሆነ አነስተው፤ አሁን ያለው የዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግስት የቀሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ብቻ መፍታቱን አስታውቀዋል።

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአሥተዳደር ዘመናቸው ለተፈፀሙ ጥፋቶች ስልጣናቸውን በይፋ መልቀቃቸውን ባሳወቁበት ጊዜ ይቅርታ መጠየቃቸውን እና በግልም ሰብኣዊ መብት ጥሰት ደረሰባቸው ግለሰቦች ካሉ ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሚችሉም አስታውቀው ‹‹አምባገነን ተብየ ልፈረጅ ግን ይገባም ስህተትም ነው ›› ሲሉም ተደምጠዋል። በግለሰቦች ላይ የሚደርሰው የግድያ ጥቃትም ከእርሳቸው የስልጣን ዘመን ይልቅ አሁን ባለው የለውጥ ጊዜ እንደሚብስ ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here