ኢትዮጵያዊው ስደተኛ በእንግሊዝ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

ተመስገን ደስታ የተባለ እና በእንግሊዝ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ኹለት ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። የ32 ዓመቱ ተመስገን በሚኖርበት አገረ እንግሊዝ ኹለት ሴቶችን በስምንት ሰዓታት ልዩነት መድፈሩን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን የበርሚንግሃም ፍርድ ቤትም የዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶበታል።

የመጀመሪያውን የመድፈር ጥቃት የፈፀመው በእንግሊዝ ሊቨርፑል ከተማ የባህር ዳርቻ ላይ ነው ያለው ፖሊስ ኹለተኛውን ጥቃት ደግሞ በበርሚንግሃም ከተማ አፓርትመንት ውስጥ መሆኑንም አስታውቋል። የቢቢሲ ዘገባ እንደሚያመለክተው ተመስገን በመጀመሪያ ምንም አይነት ጥፋት አለመፈፀሙንና ለፍቶ አዳሪ መሆኑን በመግለፅ የዕምነት ክህደት ቃሉን እንደሰጠ አስታውቋል። ዘገባው አያይዞም ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ከአጋጠማቸው ጉዳት የተነሳ ከድንጋጤ ገና ያላገገሙ ሲሆን አሁንም ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here