ከአራት ሚሊዮን በላይ ሕፃናት አስቸኳይ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል

0
745

በኢትዮጵያ የተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የሚኖሩ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት አስቸኳይ የምግብ እና የመጠለያ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ወርልድ ቪዥን ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ። ከ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፈጣን ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፀው ድርጅቱ፣ ለሰብዓዊ ቀውሱ ምላሽ ለመስጠት ቢያንስ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር (37 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር) እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

ለቀውሱ እስካሁን ወደ 288 ሚሊዮን ዶላር (8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር) የፌዴራል መንግሥት የሰጠ ሲሆን ቀሪው ከተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም መስከረም ወር ከ11 በላይ ዜጎች በኮሌራ ምክንያት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ወርልድ ቪዥን አስታውቋል። ከ 1 ሺሕ 286 በላይ ዜጎች በኮሌራ በሽታ በተመሳሳይ ወቅት ተጠቅተው እንደነበር ሪፖሪቱ ያሳያል።

ቅጽ 1 ቁጥር 51 ጥቅምት 15 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here