በምስራቅ አፍሪካ እና በየመን የሚገኙ ስደተኞችን ለመርዳት 54 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት በምስራቅ አፍሪካ አገራትና በየመን የሚገኙትን ስደተኞች አጣዳፊ የነብስ አድን ዕርዳታ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 54 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ይፋ አደረገ።

በድርጅቱ የመስራቅ አፍሪካ እና የየመን ቀጠናዊ ስደተኞችን መድረስ የተሰኘው መርሃ ግብር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና የመን 113ሽሕ ስደተኞች አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል። እንደ መንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ምስራቃዊ መተላለፊያ ተብሎ በተሰየመው መንገድ አየተገባደደ ባለው የፈረንጆች ዓመት 2019 ብቻ  160 ሽሕ ስደተኞች ከተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ አገራት የመን መግባታቸው ታውቋል።

ወደ የመን እና የመንን መተላለፊያ በማድረግ ወደ ሳኡዲ ዐረቢያ በሚደረገው ሕገ ወጥ ጉዞ ላይም በርካቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚደርስባቸው እና ህይወታቸውን እስከማጣት የሚደርስ እንግልት እንደሚያጋጥማቸው አይኦኤም አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here