ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በ13 እጥፍ አደገ

0
873

በኢንፎርሜሽ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃት ዝግጁነት እና ምላሽ መስጫ ማዕከል በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በስድስት ዓመታት ውስጥ 13 እጥፍ ዕድገት ማሳየቱን አስታወቀ። ማዕከሉ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው፤ በ2005 የነበረው የሳይበር ጥቃት በአገር ደረጃ 59 ብቻ የነበረ መሆኑን ጠቅሶ በ2011 በተደረገው ጥናት የሳይበር ጥቃቱ 791 መድረሱን አስታውቋል።

የሳይበር ጥቃት ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል ምላሽ የተሰጠባቸውን አገራዊ የሳይበር ጥቃቶች መጠን በመተንተን ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን ጥቃቶች እየቸመሩ መምጣታቸውን አስታውቋል። ከሳይር ጥቃት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ በ2012 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 113 የሳይበር ጥቃቶች እና ሙከራዎች መመዝገባቸውን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ከሪፖርቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቃቶቹ በዋናነት የሚያነጣጥሩት በመንግስት ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ እደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here