በእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ረብሻ ለማስነሳት ተሞከረ

0
1100

በእንጅባራ ዩኒቨርስቲ እሁድ ኅዳር 7/2012 ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ በዩኒቨርስቲው የተፈጠረውን ድንገተኛ የመብራት መቋረጥ ተከትሎ ረብሻ የሞከሩ ሰዎች እንደነበሩ ታወቀ። እንጅባራ ዩኒቨርስቲ እንዳስታወቀው ከመብራት መቋረጡ ጋር ተከትሎ የተወሰኑ ተማሪዎች በመጮህ እና ድንጋይ በመወርወር በተለይም ደግሞ ወደ ሕንጻዎች ድንጋይ እንደተወረወረ እና ረብሻ ለማስነሳት ሞክረው እንደነበር ታውቋል።

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማወክ የተሞከረውን ሙከራም ወቅታዊ የዩኒቨርስቲዎችን ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በተጠንቀቅ ሲጠብቁ በነበሩት የፌደራል ፖሊስ ፣ የክልሉ አድማ ብተና ኃይልና በዩኒቨርስቲው የተለያዩ አደረጃጀቶች ትብብር በሰው ላይ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

በዛሬው ዕለት ሰኞ ኅዳር 8/2012 ተማሪዎች ከቁርስ ሰዓት በኋላ ከአገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና አመራሮች ጋር ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here