ኔዘርላንድ እና ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ አብረው ለመስራት ተስማሙ

0
736

ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ በቱሪዝም ዘርፍ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ያለውን ቱሪዝም ዕድገት በተመለከተ በጋራ ለማስራት ስምምነት ላይ ደረሱ። ስምምነቱም በኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው(ዶ/ር)  በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ መካከል ተፈርሟል።

የደች መንግስት ዘርፉን ለማጎልበት፣ ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም ለቁጥጥር ስራ የሚውል 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ የተስማማ ሲሆን ለፕሮጀክቱም የሦስት ዓመታት ጊዜ ገደብ ተቀምጧል። ምክትል ልዩ መልዕክተኛው ዚጄስ ውዲስተራ በስምምነቱ ወቅት እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የምንጊዜም አጋራቸው እንደሆነችና አሁን የተፈረመው ስምምነትም 25 አስጎብኚ ድርጅቶችንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ሒሩት በበኩላቸው ከኔዘርላንድ መንግሥት ጋር የተደረሰው ስምምነት በርካታ እድሎችን የሚፈጥር እንዲሁም የግል እና የመንግሥት ድርጅቶች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስተሳስር ነውም ብላዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአስጎብኚ ድርጅቶች መካከል የሚታየውን የአቅም ክፍተትም ይሞላል ተብሏል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here