አፍሪካ የቡድን 20 አባል ለመሆን መቃረቧ ተገለጸ

0
357

እሁድ ነሐሴ 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከረዥም ጊዜ ደጅ መጥናት በኋላ አፍሪካ የቡድን 20 አባል ለመሆን ከመቸውም ጊዜ በላይ ተቃርባለች ተብሏል።

በአሜሪካ፣ ቻይናና አውሮፓውያን ድጋፍ የአፍሪካ ሕብረት በመጭው መስከረም ወር የቡድኑ አባል ሊሆን እንደሚችል ሰፊ ግምት ተሰጥቶታል።

አፍሪካ በማህበሩ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ባለፈው ዓመት በሴኔጋል ሀሳብ የቀረበ ሲሆን፤ አሜሪካ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ህብረት ሀሳቡን ሲደግፉ ቆይተዋል።

ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ከሚኖርባት አፍሪካ ብቸኛዋ የማህበሩ አባል ደቡብ አፍሪካ ስትሆን፤ ከአፍሪካ ሕዝብ በግማሽ የሚያንስ ሕዝብ የሚኖርበት አውሮፓ በአምስት አገራትና በአውሮፓ ሕብረት መወከሉ ቅሬታ ሲያስነሳ ቆይቷል።

የዓለማችን የበለጸጉ አገራት ማህበር የሆነው ቡድን 20፣ የአውሮፓ አህጉር አምስት አገራትን እና አውሮፓ ሕብረትን በመያዝ ቀዳሚ ባለ ብዙ መቀመጫ ሲሆን፤ እስያ በአምስት አገራት ተከታይ ነው።

ከአሜሪካና ካናዳ በተጨማሪ ሦስት የላቲን አሜሪካ አገራትም የማህበሩ አባል ናቸው። በቀጣይ የአፍሪካ ሕብረት 21ኛ የማህበሩ አባል ለመሆን ተቃርቧል ነው የተባለው።

የቡድን 20 ጥምረት የሆኑት 19 አገራትና አውሮፓ ሕብረት 85 በመቶ የዓለም ጠቅላላ ምርት ባለቤት እንዲሁም፤ 75 በመቶ የዓለምን ንግድ የሚዘውሩ እና ኹለት ሦስተኛው የዓለም ሕዝብ መገኛ ናቸው።

ማህበሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዋነኛ መወያያ መድረክ እየሆነ ስለመምጣቱ ይነገርለታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here