የመስራት ኢንተርፕረነርሺፕ ፕሮግራም ተከፈተ

0
233

መስራት፣ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ገበያ እና ተባባሪ አጋሮቹ መካከል ባለው ስምምነት የተደራጀ ሲሆን ለመስራት የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ማመልከቻዎች መከፈቱን ያስታውቃል።

መርሃ ግብሩ በመላው ኢትዮጵያ 100 ሁለገብ የጊግ ስራዎች እና ፕሮፌሽናል የገበያ ቦታዎችን ይደግፋል፣ ይህም ለ1 ሚሊየን ከፍተኛ ችሎታ ላላቸው ሰራተኞች እድልን ይፈጥራል። ከእነዚህ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ውስጥ 80% የሚሆኑት ወጣት ሴቶች ሲሆኑ 10% የሚሆኑት ደግሞ የተቸገሩ ወጣቶች ይሆናሉ። የዚህ ግብ አካል የሆነው የመስራት ኢንተርፕረነርሺፕ ፕሮግራም ያለምንም ወጪ ንግዶቻቸውን በፍጥነት መገንባት ለሚፈልጉ 100 የንግድ ባለቤቶች ነፃ ግብዓቶች ድጋፍን እየሰጠ ይገኛል።

መርሃግብሩ የተመረጡት ሥራ ፈጣሪዎችን በእነዚህ ዘርፍ ይረዳል-

– ምዝገባዎችን ለመሰብሰብ፣ ተጠቃሚዎች ለማስገባት እና ለማዛመድ ብጁ ስርዓት ማግኘት
– ተመራጭ ደንበኞችን እና ዒላማ ቡድኖችን ለማግኘት የግብይት ዘመቻዎችን ማዳበር እና ማስፈጸም
– ንግድዎን የሚያጎለብቱ የንግድ ድርጅቶችን አውታረ መረብ ማግኘት
– እድገትን ለማጠናከር የሚረዳ ፋይናንስ አገልግሎት
– የተለመዱ ችግሮችን ለማስወገድ እና የተሻሉ ውሳኔዎችን ለማድረግ ልምድ ካላቸው ሥራ ፈጣሪዎች የተሰጠ መመሪያ ልውውጥ ማድረግ።      
– በኢትዮጵያ ገበያ ላይ የተሻለ እይታ እና መልካም ስም እንዲያገኙ በመርዳት

መስራት ለሥራ ፈጣሪዎች ብጁ የምርት ስም ያለው የገበያ ቦታ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፣ የብቃት ማጣሪያ አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ የምስክር ወረቀቶችን በመሸለም  እና የጊግ ሠራተኞችን ለሥራ በማቅረብ ለእነዚህ ሥራ ፈጣሪዎች  የሚያስፈልጋችውን ድጋፍ ይሰጣል ።

ድጋፋችን የንግድ ልማትን፣ የፋይናንስ አቅርቦትን እና የገበያ ትስስርን ያካትታል። በተጨማሪም፣ ለጊግ ኢኮኖሚ እና ለጊግ ሰራተኞች ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና መመሪያ ልማት እናበረታታለን እና ከህዝብ ሴክተር ተዋናዮች ጋር አንድ ላይ እንሰራለን።

የብቃት መስፈርት፡

– ኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገበ ፍቃድ ላላቸው
– በፅንሰ-ሃሳብ ማረጋገጫ የተፈተነ ሃሳብ ማሳየት
– ሊሰፋ የሚችል የንግድ ሞዴልን የያዘ
– በሃሳቡ ላይ ሙሉ ጊዜ የሚሰራ ልምድ ያለው ቡድን ያላቸው
– ቢያንስ ለ6 ወራት የሚሰራ ንግድ ያለው
– ባለብዙ ጎን የገበያ ቦታ ተዛማጅ ሞዴል በኩል ሙያዊ ጊግ ስራዎችን የሚያቀርብ
– እንቅስቃሴ ፈጣሪ አገልግሎት የሚያቀርብ ወይም ልዩ እሴትን ይዞ የሚመጣ

መስራት ለአካል ጉዳተኞች፣ በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ግለሰቦች፣ ከስደት ተመላሾች እና ወጣት ሴቶች የጊግ የስራ እድሎችን ለሚፈጥሩ ልዩ ምርጫዎችን ይሰጣል።

የጊግ ስራ ምንድን ነው?

– በጊዜ የተገደበ ስራ፣ ተግባር ወይም አገልግሎት በፍላጎት የሚሰራ። የጊግ ስራ ምሳሌዎች የሚያጠቃልሉት ቢሆንም በእነዚህ ብቻ ያልተገደቡ ናቸው፤ የህጻናት እንክብካቤ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የቤት እና የቢሮ ጽዳት፣ የግራፊክ ዲዛይን እና በቤት ላይ የተመሰረተ የጤና እንክብካቤ። ከመደበኛ የቅጥር ውል ውጭ እነዚህን አገልግሎቶች በጥሪ ላይ የሚያቀርቡት ባለሙያዎች “የጊግ ሠራተኞች” ይባላሉ።

የእርስዎ ጅምር ንግድ ስራ በጊግ ስራዎች ላይ የሚሰራ ነው?  ከሆነ መስራት ይደግፋችኋል።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች፡ በእዚህ ያመልክቱ

ምልክት የተደረገባቸው ቀናት፡-

የማመልከቻ ገደብ፡ መስከረም 19, 2016

ለማንኛዉም አይነት ጥያቄዎች [email protected] ላይ ማቅረብ ይቻላል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here