የነሐሴ ወር አገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 28 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

0
475
አርብ መስከረም 11 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በነሐሴ ወር የአገር አቀፍ የዋጋ ግሽብት 28 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ በወሩ ዉስጥ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት የምግብ ዕቃዎች ዋጋ 26 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ መያዙን የገለጸ ሲሆን፤ ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ 30 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ መያዛቸውን ገልጿል፡፡
በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር ከነበረት 28 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 28 ነጥብ 2 በመቶ መውረዱንም አዲስ ማለዳ ከአገልግሎቱ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here