በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ነገ ይጀመራል

0
187

ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከነገ መስከረም 29/2016 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ፈተናውን በ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ የነበሩና መልቀቂያ ፈተናውን ሳይወሰዱ የቀሩ ከ11 ሺሕ በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱት፤ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ45 ቀናት በላይ የማጠናከሪያ ትምህርት ሲወስዱ መቆየታቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ነገ የሚጀመረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እስከ ጥቅምት 02/2016 ድረስ፤ በኣክሱም፣ በዓዲግራት፣ በመቐለና በራያ ዩኒቨርስቲዎች ብቻ እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡

በትግራይ ክልል በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በክልሉ በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ፈተናው ላለፉት ሦስት ዓመታት ሳይሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here