የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት (ከ50% በላይ) ያመጡት ተማሪዎች ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ

ከ169 ሺሕ በላይ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች ማለፊያ ውጤት ያመጡት 480 ተማሪዎች ናቸው

0
230

ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ውጤት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በተፈጥሮ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡት 356 ሺሕ 878 ተማሪዎች ውስጥ 22 ሺሕ 974 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ በማህበታዊ ሳይንስ ከተፈተኑ 488 ሺሕ 221 ተማሪዎች ውስጥ 8 ሺሕ 250 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በአጠቃላይ ከተፈተኑ ተማሪዎች ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት 27 ሺሕ 267 መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ከአጠቃላይ ተፈታኞች ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ የሚይዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የተመዘገበዉ ከፍተኛ ውጤት ከተፈጥሮ ሳይንስ 649 በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 በደብረ ማርቆስ ከተማ መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ለፈተናው ከተቀመጡ ከ169 ሺሕ 502 የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች ውስጥ የማለፊያ ውጤት ያመጡት 480 ተማሪዎች መሆናቸውንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here