“ውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታቸውን እስከ ጥቅምት 5 ድረስ ማመልከት ይችላሉ” የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

0
310

ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገጽ ላይ እየገቡ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የፈተና ውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው eaes.et ላይ እስከ ጥቅምት 5/2016 ከቀኑ 11:30 ድረስ ብቻ ማቅረብ እንደሚችሉም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ብቻ ሳይሆን፤ ኦርጂናሉ ሠርቲፊኬት እስኪደርሳቸው ድረስ ጊዜያዊ ሠርቲፊኬታቸውን በሶፍት ኮፒ መውሰድ ወይንም ማተም እንደሚችሉም አገልግሎቱ ገልጿል።

በዚህም መሠረት ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡

👉 በዌብ ሳይት፡- eaes.et

👉 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284

👉 ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል “ውጤት እንገልጻለን” ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁም መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

በ2015 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱት 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ የማለፊያ ወይም ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡት 27 ሺሕ 267 ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here