በወልቂጤ ከተማ ተጥሎ የነበረዉ የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ተደረገበት

0
145

ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት የሰዓት ገደብ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር እና በአካባቢው አሁናዊ የጸጥታ ኹኔታ አንጻራዊ መሻሻል እየመጣ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ መልኩ ማድረግ እንዲችል የሰው፣ የባጃጅና ሆቴሎች ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት ከዛሬ ጥቅምት 21/ 2016 ጀምሮ የእንቅስቃሴ ሰዓት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ያስታወቀ ሲሆን፤ ከዚህ ውጪ የተለየ እንቅስቃሴ የሚያደርግ በማንኛውም አካል ላይ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስደው ሕጋዊ እርምጃ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here