ኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በኪንሻሳ መጠነኛ ጉዳት ደረሰበት

0
1494

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ኤር ባስ ኤ350-900  የተባለው አውሮፕላን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለፀ። አውሮፕላኑ በኪንሻሳ ንጂላይ አየር ማረፊያ ላይ ንብረትቱ የቱርክ አየር መንገድ ከሆነው ኤር ባስ ኤ330-200ኤፍ ከሆነ አውሮፕላን ጋር በማኮብኮቢያ ሜዳ ላይ በመጋጨታቸው እንደሆ ለማወቅ ተችሏል።

በአየር ማረፊያው ማኮብኮቢያ እና መንገደኞች ወርደው ወደ ሻንጣ መቀበያው ለመሔድ የአውቶብስ ጉዞ በሚያደርጉበት ቦታ ላይ ኹለቱ አውሮፕላኖች እንደተጋጩ መረጃዎች አመላክተዋል። በግጭቱም የኢትየጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው አውሮፕላን የኋላ ክንፍ ( አግዳሚ ስታብላይዘር) ላይ መጠነኛ ጉዳት መጣመም እና መታጠፍ የመሰለ ጉዳት  እንደደረሰም ለማወቅ ተችሏል። ይህም የቱርክ ዕቃ ጫኝ የሆነው አውሮፕላን ክንፍ የኢትዮጵያ አየር መንገዱን አውሮፕላን የኋላ ክፍል በመግጨቱ ነው ተብሏል። በተፈጠረው ክስተትም በሰው ላይም ሆነ በመንገደኞች ንብረት ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ለማወቅ ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here