ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ኤር ባስ ኤ350-900 የተባለው አውሮፕላን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለፀ። አውሮፕላኑ በኪንሻሳ ንጂላይ አየር ማረፊያ ላይ ንብረትቱ የቱርክ አየር መንገድ ከሆነው ኤር ባስ ኤ330-200ኤፍ ከሆነ አውሮፕላን ጋር በማኮብኮቢያ ሜዳ ላይ በመጋጨታቸው እንደሆ ለማወቅ ተችሏል።
በአየር ማረፊያው ማኮብኮቢያ እና መንገደኞች ወርደው ወደ ሻንጣ መቀበያው ለመሔድ የአውቶብስ ጉዞ በሚያደርጉበት ቦታ ላይ ኹለቱ አውሮፕላኖች እንደተጋጩ መረጃዎች አመላክተዋል። በግጭቱም የኢትየጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው አውሮፕላን የኋላ ክንፍ ( አግዳሚ ስታብላይዘር) ላይ መጠነኛ ጉዳት መጣመም እና መታጠፍ የመሰለ ጉዳት እንደደረሰም ለማወቅ ተችሏል። ይህም የቱርክ ዕቃ ጫኝ የሆነው አውሮፕላን ክንፍ የኢትዮጵያ አየር መንገዱን አውሮፕላን የኋላ ክፍል በመግጨቱ ነው ተብሏል። በተፈጠረው ክስተትም በሰው ላይም ሆነ በመንገደኞች ንብረት ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ለማወቅ ተችሏል።



