ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 18/2012

0
900

1-የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በድህረ ፈቃድ ቡድን አማካኝነት በ421 ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር አድርጎ 127ቱ በተለያየ ደረጃ የአዋጅ ጥሰት የታየባቸው ሲሆን 67ቱ ድርጅቶች ፈቃዳቸው የተሰረዘ ፣28ቱ በድጋሚ በክትትሉ ወቅት ያልተገኙ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 199 በሕግ አግባብ እየሰሩ መሆናቸውን ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

2-የግንባታ ስራቸው ተቋርጦ የነበረው 107 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነቀምት-ቡሬ የመንገድ ግንባታ ስራን መልሶ ለማሰጀመር ጨረታ መውጣቱን  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገልጿል።የግንባታ ስራቸው የሚጀመሩት ኹለት ኮንትራቶች ነቀምት- እንዶዴ (ኮንትራት አንድ) እና አጋምሳ-ቡሬ (ኮንትራት ሶስት) መሆናቸው ተጠቅሷል።በወጣው ጨረታ መሰረት አስፈላጊው የቴክንክና የፋናንሻል ግምገማ ተካሂዶ የስራ ተቋራጩ እንደሚታውቅና በቀጥይ ወደ ግንባታ እደሚሽጋገር ታውቋል።(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

……………………………………………………………..

3-የሐንጋሪ መንግስት በ1960ዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀረፁ ባህላዊና ታሪካዊ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስረክቧል። ከ3 ሺሕ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው የፊልም ክሮች፤ ከ40 ሰአታት በላይ ድምፅ፤ ከ100 በላይ ምስሎችንና ከ200 ገፅ በላይ ፅሁፎችን ቀርፀው የነበረ ሲሆን በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት በሚገኘው በሐንጋሪ ሳይንስ አካዳሚ የሙዚቃ ጥናት ተቋም ውስጥ የባህላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜዎች ቤተ መዛግብት ተቀምጦ እንደነበር ታውቋል።በኢትዮጵያ የሐንጋሪ አምባሳደር አቲላ ኮፓኒ ከኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ሂሩት ካሳው(ዶ/ር) በነበራቸው  ቆይታ ታሪካዊ ተንቀሳቃሽ ምስሎቹን አስረክበዋል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

4-የመንግስት የልማት ድርጅቶች ብድራቸውን በሚገባ እየመለሱ እንዳልሆነ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታውቀ።የልማት ድርጅቶቹ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 245 ሚሊዮን ብር መመለስ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም የመለሱት ግን 61 ነጥብ 89 ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን ተቋማቱ ከዚህ በፊት ለመሰረተ ልማት ማስፋፊያ እና መሰል ስራዎች ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተበደሩትን ብድር የመለሱት መክፈል ካለባቸው 25 በመቶን ብቻ መሆኑ ተገልጿል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

……………………………………………………………..

5- በመንግስት ይዞታ ስር የሚገኙ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች ከወራት በኋላ ወደ ግል እንደሚዞሩ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታው እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) አስታወቁ። በአሁን ሰዓት በመንግስት ስር ያሉ 13 የስኳር ፋብሪካዎች የቴክኒክ፣ የዋጋ፣ የማህበራዊና የአካባቢ ጥበቃ ጥናቶች እየተከናወነላቸው እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን ጥናቱ በመጭው ታህሳስ ወር ሲጠናቀቅ ስድስቱ ወደግሉ እንደሚዞሩ ተናግረዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………………………..

6-የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከ13 የሕዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበራት ጋር በፍጥነት መንገዶች ላይ የጊዜው እየጨመረ የመጣውን  የትራፊክ አደጋ እና  በፍጥነት መንገድ አጠቃቀም ዙርያ ቅዳሜ ኅዳር 20/2012 በሞናርክ ሆቴል ወይይት እንደሚደረግ አስታውቋል።በውይይቱም ላይ የትራንስፖርት ባለስልጣን ኃላፊዎች እና የ13 ሕዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማኅበራት የቦርድ ሰብሳቢዎች እንደሚገኙ ታውቋል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

7-ኹለት የሲዳማ ተቃዋሚ ፖርቲዎች «በጋራ ለመስራት ያስችለናል» በማለት «ቅንጅት»በሚል ስያሜ  መዋሐዳቸውን አስታወቁ። ቅንጅት የመሰረቱት ኹለቱ ፓርቲዎች የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሲብዴፓ) እና የሲዳማ ሐድቾ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሲሐሕዴድ)ሲሆኑ ፓርቲዎቹ በአካባቢያዊና አገራዊ የፖለቲካ አንቀስቃሴ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ማድረጋቸውን የየድርጅቶቹ አመራሮች ገልጸዋል። በተለይም በተያዘው ዓመት በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በአንድ የምርጫ ምልክት ለመወዳደር የሚያስችላቸውን ቅደመ ዝግጅት በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።(ዶቼ ቬለ)

……………………………………………………………..

8- ነገ የሚጀመረውን 13ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ መደበኛ የመሪዎች ስብሰባ ለመታደም የአባል አገራቱ መሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።(ኢቢሲ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here