ምንጭ፡-ዓለም አቀፍ የደስተኛነት ሪፖርት 2018 (እ.ኤ.አ)
156 አገራትን በደስተኛነት ደረጃ 117 አገራትን ደግሞ በስደተኞቻቸው የደስተኝነት ደረጃ የመደበው ዓለም አቀፉ ደስተኛነት ሪፖርት ላይ ፊላንድ የዓለም ደስተኛዋ አገር በመባል አንደኛ ደረጃን ተቀዳጅታለች። ባለፈው ወር በወጣው ይህ ሪፖርት ላይ ኖርዌይ እና ዴንማርክ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ያገኙ ሲሆን ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ ደግሞ ካለፈው ዓመት አራት ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 18ተኛ ደረጃ ላይ ልትቀመጥ ችላለች። ጋላፕ በተባለ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ጥናት-ተኮር የአፈፃፀም-አስተዳደር አማካሪ ድርጅት ከ2015-2017 በሚሠራቸው ዳሰሳዎች መሠረት የሚዘጋጀው ይህ ሪፖርት ከየአገራቱ መጠይቆችን ለሦሶት ሺህ ግለሰቦች በማስሞላት ልኬቱን ያዘጋጃል። የአገራት ጥቅል ምርት፣ የእድሜ ጣሪያ፣ ለጋስነት፣ የማኅበራዊ ድጋፍ ስርዓት፣ የነፃነት እና የሙስና ደረጃዎች ለደረጃ ልኬቱ ግብአት ሆነዋል። ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች 20ኛ ደረጃን ያገኘች ሲሆን ከዓለም ደግሞ 127ኛ ደረጃን በመያዝ ከግብፅ፤ ሞዛምቢክ እና ኬኒያ ኋላ ተሰልፋለች።
ቅጽ 1 ቁጥር 3 ኅዳር 22 ቀን 2011



