ባሳለፍነው ሳምንት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ተዋሕደው መቀጠል የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈራራማቸው ይታወሳል። ይህም በማሕበራዊ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
ይህን ተከትሎ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች ከተስተናገዱ አስተያየቶች መካከል ‹‹በመርህ ደረጃ የፓርቲዎች መቀራረብ የሚደገፍ ነው ይሁንና ጠብመንጃ የተማዘዙት ሁለት ፓርቲዎች ምንም ልዩነት የለንም ሲሉ መስማት የሚያሳምን አይመስልም›› የሚሉ ይገኙበታል። በተጨማሪም ‹‹ለአንዲት አገርና ሕዝብ ከሆነና ሌላ ስውር አጀንዳ ወይም ስልጣንን መከታ አድርጎ እንደ ሌሎቹ የሕዝብን ሀብት ለመቀራመት ምኞት ከሌላቸው ለምን እንደዚህ በጋራ አይቆሙም?›› የሚል አስተያየትም ተስተናግዷል።
ከነዚህም በተጨማሪም ‹‹እዚህ አገር በጣም የተሳካው ውሕደት ቁርስና ምሳ ተጣምረዉ የፈጠሩት ‘ቁምሳ’ የተሰኘ ቃል ነው ሲሉ የተረቡት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁምሳ የመንግስት ቢሮዎች ውስጥ በተለይ ብዙ አባላት ያሉት ነው ሲሉም የፖለቲካ ፓርቲ ዌምሌላ ማህበር አስመስለውታል።
ቅጽ 1 ቁጥር 3 ኅዳር 22 ቀን 2011